Fana: At a Speed of Life!

በውጭ ለሚኖሩ 2ኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን የቀረበው ጥሪ አቅማቸውን ለሀገር እንዲያውሉ ይረዳል- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ለሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን የቀረበው ሀገራዊ ጥሪ በተለያየ ሀገር እና ዘርፍ ያካበቱትን ልምድና ሌሎች አቅሞች ለሀገር ውስጥ ልማት ለማዋል የሚችሉበትን ዕድል እንደሚፈጥር ምሁራን አስገነዘቡ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውጭ ለሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሦስት ዙር ወደ ሀገራቸው በመምጣት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ፣ ባሕሏንም እንዲያውቁ እና በሀገራቸውም ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ በቅርቡ ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡
 
ይህን ተከትሎም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንዳሉት÷ የቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ጥሪው የቀረበላቸው ወገኖች አቅማቸውን ለሀገራቸው እንዲያጋሩ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡
 
የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ተሻለ ሰብሮ (ዶ/ር) ጥሪ የተደረገላቸው ወገኖች ሀገራቸው ያለችበትን ደረጃ ማየት ቀዳሚ ተግባራቸው ሊያደርጉ ይገባል፤ ለዚህ ደግሞ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡
 
ጥሪው በውጭ የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ሀገር በተለያዩ ዘርፎች ያካበቷቸውን ልምዶችና ሌሎች አቅሞች ለሀገር ውስጥ ልማት ማዋል የሚችሉበትን ዕድል እንደሚፈጥርም ነው ያስረዱት፡፡
 
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሐብት ተመራማሪና መምህር የሆኑት ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የሀገራዊ ጥሪው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
 
ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ አቅምና የምርምር ውጤቶችን ለሀገራቸው ማጋራት የሚችሉበት መልካም አጋጣሚ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
 
ባሉበት ሀገር አምባሳደር መሆናቸውን ተገንዝበው የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ኢትዮጵያ መሳብ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል።
 
በአሸናፊ ሽብሩ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.