Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የደኅንነት ጥበቃ ስልጠና ወስደው ለተመለሉ ፖሊስ ኦፊሰሮች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በሕዝብ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ የቪአይፒ ደኅንነት ጥበቃ ስልጠና ወስደው ለተመለሱ 72 የፖሊስ ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጓል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ጀኔራል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል÷ ስልጠናው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና በቻይና የህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር  መካከል የኢትዮጵያ ፖሊስ ኦፊሰሮችን አቅም በስልጠና ለማጠናከር የተደረሰው ስምምነት አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ስልጠናው ፌዴራል ፖሊስን የተሻለ የቪአይፒ ጥበቃ እና የሞተር ኬድ እጀባ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ገልፀዋል።

በስልጠናው ከቻይና የተወሰደውን ተሞክሮ ወደ ሀገር ውስጥ በማምጣት ለክልል ፖሊስ ኦፊሰሮች እና ለምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ ተቋማት አቅም የሚሆን የስልጠና ማዕከል እንደሚከፈትም አመላክተዋል፡፡

የፖሊስ መኮንኖቹ በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በብቃት እንዲተገብሩም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዋን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም ቦርድ አባል ከሆነች ጊዜ ጀምሮ በሕዝብ ደኅንነት ዙሪያ ከቻይና ጋር ስትሰራ መቆየቷን እንዳነሱ ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.