Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ቅርሶችና የቱሪዝም መዳረሻዎች እየተጠገኑ ነው – ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የቅርሶችና የቱሪዝም መዳረሻዎች የጥገና ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሐብታሙ አበበው እንዳሉት÷ ለጥገናና መልሶ ማልማት ሥራ የሚውል 5 ሚሊየን የሚጠጋ ብር ለክልሉ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ባለስልጣኑ የክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በአክሱም፣ ዓድዋ፣ ዓዲ ግራት፣ ተምቤን፣ ገርዓልታ፣ ውቅሮና አልነጃሽ አካባቢዎች የሚገኙ ጥገና የሚያስፈልጋቸው 21 ቅርሶችና መዳረሻዎች የጥገናና ማልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የብቃት ማረጋገጥ እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር  የማነ ገደሉ አረጋግጠዋል፡፡

ከዘርፉ መገኘት ያለበትን ጥቅም ለማሣደግም ሰላምን ማጽናት እና መልካም ገጽታ ማጎልበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.