Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል 3ኛውን ዙር የተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ሦስተኛውን ዙር የተባባሪ አካላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በፊልቱ ከተማ የዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና 88 ሰልጣኝ ተባባሪ አካላትን ማሳተፉ ተገልጿል፡፡

ተባባሪ አካላቱም ከክልሉ ዳዋ እና ሊበን ዞኖች 11 ወረዳዎችን በመወከል ተሳታፊዎች ሆነዋል ነው የተባለው፡፡

በስልጠናው ለተባባሪ አካላቱ ስለ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች፣ ስለ ኮሚሽኑ ዓላማ እና መርሆች እንዲሁም በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ላይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ግንዛቤን የሚፈጥሩ ገለፃዎች ተደርጎላቸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በዞናቸው በሚገኙ ወረዳዎች በኮሚሽኑ ከተለዩት የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ ሂደቱ ተዓማኒ እንዲሆን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉም ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.