Fana: At a Speed of Life!

በጋራ የመልማት መርህን የተከተለው የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የህልውና ጥያቄ ነው – አምባሳደር መለስ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰጥቶ መቀበል እና በጋራ የመልማት መርህን የተከተለው የኢትዮጵ የባሕር በር ጥያቄ የህልውና ጥያቄ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

አምባሳደር መለስ (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ÷የኢትዮጵያን የህልውና ጥያቄ ተከትሎ በዓረብ ሊግና በግብጽ በኩል የሚወጡ መረጃዎች ከእውነታ የራቁና ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘቡ ናቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት ቀናት የታየው መነቃቃት የዲፕሎማሲ አውደ ርዕይን በተሻለ ሁኔታ ለማክበር ፍንጭ የሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥር 2 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመካሔድ ላይ ያለው የዲፕሎማሲ ሳምንት በበርካታ ዜጎችና ተቋማት እንዲሁም በዲፕሎማቶች እየተጎበኘ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አወደ ርዕዩ ወቅታዊውን የሀገራችን የባለብዙ ወገንና ሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ስኬትና ተግዳሮት ያመላከተ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

አውደ ርዕዩ ለጎብኚዎች የተሻለ ግንዛቤ እንደፈጠረ በተሰጠው ግብረ መልስ ማረጋገጥ መቻሉን ጠቁመው÷በቀጣይ መሰል አውደ ርዕይ ጎልብቶ እንዲዘጋጅ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል።

በፍሬህወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.