ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል፡፡
ዩዌሪ ሙሴቬኒ የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባዔን በማስተናገዳቸው እና ላካሄዱት የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ውይይቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አመሥግነዋል፡፡