ሮማኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሮማኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሮማኒያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁሊያ ፓታኪ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ ፥ ኢትዮጵያ እና ሮማኒያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ታሪካዊ እንዲሁም ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል።
አምባሳደር ጁሊያ ፓታኪ በበኩላቸው ፥ ሮማንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም፣ በልማት፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ያላትን ግንኙነት ለማሳደግና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ትብብር ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ ፥ ሮማኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት እና በልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ የጀመረችውን አዲስ ስትራቴጂያዊ ጅምር ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!