Fana: At a Speed of Life!

ዴንማርክ የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ የልማት ኮርፖሬሽን እና የዓለም የአየር ንብረት ፖሊሲ ሚኒስትር ዳን ዮገንሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት አላት፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የኢትዮጵያን ተግባራዊ ጥረት አብራርተው ፥ በሀገር አቀፉ አረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ባለፉት አራት ዓመታት በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።

ይህ ተግባር ኢትዮጵያ ከካርቦን ነፃ የሆነች ፕላኔት እንድትኖር ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተው ÷ መንግስት ተጠያቂነትን ለማስፈንና የሀገሪቱን ሰላም ለማጠናከር እያደረገ ያለውን ጥረት ጠቅሰዋል።

የፌዴራል መንግሥት ተጠያቂነትንና እርቅን ለማረጋገጥ ሁሉን አቀፍ የሽግግር የፍትሕ ፖሊሲ ቀርጾ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

ኢትዮጵያ ለጀመረችው አስደናቂ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ባለድርሻ አካላት ተጨባጭ ድጋፍ እንዲያደርጉም አቶ ደመቀ ጠይቀዋል።

ዳን ዮገንሰን በበኩላቸው ፥ ሀገራቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለመደገፍ ዴንማርክ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.