ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን ፓርቲው ገምግሟል – አቶ አሕመድ ሺዴ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ እንቅስቃሴዎችን እያደረገች እንደምትገኝ የብልጽግና ፓርቲ መገምገሙን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አሕመድ ሺዴ ገለጹ።
አቶ አሕመድ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ በዲፕሎማሲው መስክ የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨትን ተከትሎ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያለው ግንኙነት መሻሻል አሳይቷል።
በዚህም ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
በዘርፉ ኢትዮጵያ ነባር ግንኙነቶች ከማጠናከር ባለፈ አዳዲስ ግንኙነቶችን ለመፍጠር እየሰራች መሆኑንም አቶ አሕመድ አመላክተዋል።
በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።
በዚህም ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ሳዑዲ ዓረቢያ እና ሌሎች የገልፍ ሀገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተሰሩ ሥራዎች በመልካም ጎን ተገምግመዋል ነው ያሉት።
ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር በተደረሰ ስምምነት መሰረትም ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ አራምኮ በቅርቡ በኢትዮጵያ በነዳጅ ላይ መስራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የበለጠ ለመቀራረብ በሚያስችላት ተግባራት ላይ በትኩረት እየሰራች እንደምትገኝም አቶ አሕመድ ሺዴ አንስተዋል።
በምስክር ስናፍቅ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!