የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የሥራ አጥነትን ለመቀነስ በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስገነዘበ፡፡
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የሥራ አጥነትን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ተስፋዬ ይገዙ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግርም÷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዋጋ ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተፈተኑ ነው ብለዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋትና የሥራ አጥነትን ለመቀነስም ሁሉም መተባበር አለበት ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ገሌቦ ጎልቶሞ በበኩላቸው÷ የምርት አቅርቦት እጥረት መኖርና የሥራ እንቅስቃሴውም ወጥ አለመሆን ለኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ሥራ ማነቆ እንደነበር አንስተዋል።
በመሆኑም በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡
በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመትም ለ 62 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡
በማህሌት ኡኩሞ እና በመለሰ ታደለ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!