በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረው የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የፓርቲ የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “ላለፉት አራት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቀናል” ብለዋል፡፡
በግምገማው ከሩብ አመቱ አፈጻጸም በተጨማሪ በአንደኛው ሩብ አመት ግምገማ ላይ የተሰጡ ማረሚያዎችና መመሪያዎች አፈጻጸም መርምረናልም ነው ያሉት።
በዚሁ መሠረት የመጪዎቹን ሩብ አመታት የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡