Fana: At a Speed of Life!

በመኽር የተገኘው የስንዴ ምርት በበቂ ሁኔታ ወደ ገበያ እንዲደርስ ክትትል እየተደረገ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፋት እየለማ የሚገኘው የስንዴ ምርት ለሸማቹ ተደራሽ የሚሆንባቸውን ክትትሎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራበት እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ለማ ፥ በስንዴ ምርት የሀገር ፍጆታን በአግባቡ እንዲሸፈን ከማድረግ በተጨማሪ ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

መኸርን ጨምሮ በበጋ መስኖ የሚለማው ስንዴ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልና ገበያን ማረጋጋት እንዲችል አቅጣጫ መዝርጋቱም ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን ምርት የማሳደግ ስራዎችም እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.