Fana: At a Speed of Life!

ከተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 01፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።
 
በሚኒስቴሩ የመሠረተ ልማትና አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሄኖክ አበበ ባለፉት ስድት ወራት በተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስር ማምረት ከጀመሩ ድርጅቶች የተለያዩ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል።
 
በዚህም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መቻሉን ጠቅሰው፤ ከተላኩት ምርቶች መካከል የአቮካዶ ዘይት እና የአኩሪ አተር ዱቄት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ አብራርተዋል።
 
ቻይና እና የተለያዩ አውሮፓ ሀገራት ዋና ዋና የምርቶቹ መዳረሻ እንደነበሩም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የአቮካዶ ምርት ከማቀነባበር ጋር በተያያዘ የህገ ወጥ ደላሎች ጣልቃ ገብነት እና የምርቱ ወቅታዊነት ችግር እንዲሁም በቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ሪች ላንድ አግሮ ፕሮሰሲንግ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ድርጅቱ በሙሉ እቅሙ እንዳያመርት ተጽእኖ ማሳደሩንም አንስተዋል፡፡
 
በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ የግብርና ሚኒስቴር ባወጣው የኮንትራት ፋርሚግ አዋጅ መሰረት የግብአት አቅርቦት የትስስር ሰንሰለትን የማጠናከር፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎቹን የማምረት አቅም ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
 
የሃይል አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ከፓርኮቹ የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ የገቢ መጠን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም የዴስክ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.