በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ረዳት ዋና ፀሐፊ እና አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገለፁ።
ረዳት ዋና ፀሐፊው ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በተመለከቱበት ወቅት ነው።
በፓርኩ የሚገኙ ሱፍሌ እና ጄጄ ኩባንያዎችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት መመልከታቸው ተገልጿል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የፓርኩንና የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች በተለይም ከስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ፣ ከገበያ ትሰስር እና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ጋር የተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ራሚዝ (ዶ/ር) በበኩላቸው በፓርኩ የተመለከቱት የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልፀው፤ በተለይም ኮርፖሬሽኑ ለሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች የሰጠውን ልዩ ትኩረት አድንቀዋል፡፡
የአርሶ አደሮች የገበያ ትስስር፣ የወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የወጪ ንግድ ላይ እየተከናወኑ ያሉት አበረታች ስራዎች ሀገሪቱ የያዘችውን የኢንዱስትሪያላይዜሽንና የምዕተ ዓመቱን ግብ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ትልቅ አቅም መሆኑን አንስተዋል።
ከምልከታው ባሻገርም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተመድ ጋር በቅርበት መስራት በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት መደረጉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!