Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም የቱኒዚያው ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ሀቻኒ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

 

እንዲሁም የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቲ ዳይ ሺሜዬ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በበረከት ተካልኝ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.