Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት አራተኛውን የግብርና ልማት የግምገማ ሪፖርት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ አጠቃላይ የግብርና ልማት ፕሮግራም መሪነታቸው በፕሮግራሙ በየሁለት ዓመቱ ከሚቀርበው የግምገማ ሪፖርት አራተኛውን ለኅብረቱ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥት አቅርበዋል።

የአፍሪካ አጠቃላይ የግብርና ልማት ፕሮግራም ለአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ ሀብት ፈጠራ፣ የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት፣ የምጣኔ ሀብት እድገት እና ብልጽግና የፓሊሲ ማዕቀፍ ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ዕድገት የሪፖርታቸው አካል በማድረግ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.