Fana: At a Speed of Life!

ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት ትምህርት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት ትምህርት ላይ መሥራትና ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡
 
“ጥራት ያለው ትምህርት ለአፍሪካውያን” በሚል መሪ ሐሳብ የፓን አፍሪካ ወጣቶች ኅብረት ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
 
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በጉባዔው ማጠቃላያ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ጥራት ያለው ትምህርት ለአፍሪካውያን ተደራሽ ማድረግ ችግሮችን ለመፍታት፣ ኢኮኖሚን ለማሳደግ፣ ፈጠራን ለማስፋፋት፣ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም ቁልፍ መሠረት ነው ብለዋል፡፡
 
ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣትም ትምህርት ላይ መስራትና ኢንቨስት ማድረግ ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
 
ለአፍሪካ ወጣቶች ዘመኑን የሚመጥን ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ማድረግ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን ለመፍታት እንደሚያስችልም አመላክተዋል፡፡
 
የአፍሪካ ወጣቶች ኅብረት ዋና ፀሐፊ አሕመድ ቢኒንግ በበኩላቸው÷ እንደ አኅጉር ዘመኑን የሚመጥን፣ ጥራት ያለው፣ ዘላቂና ሁሉን አካታች የትምህርት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል።
 
ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ወጣቶችና ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ጉባዔው ጥራት ያለው ትምህርት ለአፍሪካውያን ተደራሽ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክሮ ለአፍሪካ ሀገራት የሚደርስ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.