Fana: At a Speed of Life!

ከህዝብ ጥያቄ አንጻር አሁንም በርካታ ስራዎች አሉብን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሰባት ወራት በርካታ ያሳካናቸው እና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከህዝብ ጥያቄ አንጻር አሁንም በርካታ ክፍተቶች እና ርብርብን የሚጠይቁ ስራዎች አሉብን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ካሉ አመራሮች ጋር የስራ ግምገማ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካን አዳራሽ መካሄድ መጀመሩን አስፍረዋል።

ባለፉት ሰባት ወራት በርካታ ያሳካናቸው እና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከህዝብ ጥያቄ አንጻር አሁንም በርካታ ክፍተቶች እና ርብርብን የሚጠይቁ ስራዎች አሉብን ነው ያሉት፡፡

“በሰባት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማችን መፈጸም ሲገባቸው ያልተፈጸሙ ስራዎች፣ ጉድለቶቻችን እና መንስኤዎቻቸውን በመለየት የማስተካከያ አቅጣጫ በማስቀመጥ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እንዲሁም መልካም አፈጻጸማችንን በማላቅ በቀሪ ወራት ተጨማሪ አቅም ፈጥረን ለተሻለ ዉጤት የምንዘጋጅበት መድረክ ይሆናል” ሲሉም አክለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.