አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዩኒቨርሲቲ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙዌኔ ዲቱ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና የሙዌኔ ዲቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሺባንጉ ሙአምባ ኢኖሰንት (ፕ/ር) ፈርመዋል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ በአቅም ግንባታ በረጅም እና በአጭር ጊዜ ስልጠና ላይ በትብብር እንደሚሰሩ መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ዩኒቨርሲቲዎቹ ለስምምነቱ ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት አረጋግጠዋል።