Fana: At a Speed of Life!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ በሚያስችሉ ዘርፎች የሚደነቅ ስራን እያከናወነ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እያከናወነ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት (ፋኦ) የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሞዲዚ ገለጹ።

ዩኒቨርሲቲው በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ያለማውን ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የእንሰት ዝርያ አስተክሏል።

በተከላ መርሐ ግብሩ የተገኙት ፋራይ ዚሞዲዚ÷ ፋኦ እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ዘርፎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው 17 የጥናትና ምርምር ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ግርማ ጥላሁን (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በተስፋየ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.