Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታክስ ሕግ ተገዥነት ንቅናቄ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታክስ ሕግ ተገዥነት ንቅናቄ እና የግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነ ስርዓት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እንዲሁም ግብር ከፋዮችና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ አርቲስቶች እና ስፖርተኞች የግብር አምባሳደር ሆነው እንደሚመረጡ የተገለጸ ሲሆን፤ በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ታማኝ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች ሽልማት እና እውቅና እንደሚሰጣቸውም ተመላክቷል።

የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ ግብር በመክፈል ለሀገር ታማኝነትን ማሳየት ይገባል ብለዋል፡፡

በክልሉ ከሚያገኙት ገቢ በታማኝነት ለመንግሥት የሚገባውን በመክፈል የኢኮኖሚ ድጋፍ የሆኑ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮችንም አመስግነዋል፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ በበኩላው÷ በየጊዜው እያደረገ ለሚመጣው የሕዝብ የልማት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ኢኮኖሚ ለመፍጠር የገቢ አማራጮችን አሟጦ መሰብሰብ እንደሚስፈልግ አስገንዝበዋል።

ክልላዊ ወጪን ከ75 በመቶ በላይ ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.