Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኬንያ የነበራቸውን የቀደመ ግንኙነት የሚያጠናክር ሥራ እየተሰራ ነው – አምባሳደር ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት በኩል ኢትዮጵያና ኬንያ የነበራቸውን የቀደመ ግንኙነት የሚያጠናክር ሥራ እየተሰራ ነው ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡
 
ሀገራቱ ረጅም ዕድሜ ያለው ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ግንኙነቱ እስከ ወታደራዊ ውል ድረስ የዘለቀ እንደነበር አንስተዋል፡፡
 
ወታደራዊ ውሉ ኢትዮጵያ ችግር ሲገጥማት የኬንያ ወታደር ለኢትዮጵያ እስከ መዋጋት እንዲሁም ኬንያ ችግር ሲገጥማት የኢትዮጵያ ወታደር ለኬንያ እስከ መዋጋት የሚደርስ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
 
በሌላ በኩልም ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ሰፊ ድንበር የምትጋራ መሆኗን ጠቅሰው፤ በድንበር አካባቢ ምንም አይነት የሰላም እጦት ሀገራቱ ገጥሟቸው እንደማያቅ ተናግረዋል።
 
ይህንንም ጠብቆ ለማስቀጠል የሚኒስትሮች ጥምር ምክር ቤት እንደነበራቸው አውስተዋል፡፡
 
ይሁንና ይህ ትልቅ ፋይዳ ያለው ጥምር ምክር ቤት ላለፉት ሰባት ዓመታት ተቋርጦ እንደነበር ገልጸው፤ ጥምር ምክር ቤቱ በዚህ ወር የጋራ ስብሰባውን በማድረግ የተለያዩ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን እንደተፈራረመ ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም በፀጥታ፣ በቱሪዝም፣ በግብርና እና ኤሌክትሪክን ጨምሮ ሀገራቱ በሰባት የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን አብራርተዋል፡፡
 
የመግባቢያ ስምምነቱን ተከትሎም የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታ ጉዳይን በተመለከተ ከኬንያ አቻቸው ጋር እንደሚመክሩ ጠቁመዋል፡፡
 
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግርና ወደ ፊት ለመስራት የታሰቡትን ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ ለመስራት አጋዥ ይሆናል ብለዋል አምባሳደር ባጫ፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.