አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በኢትዮጵያ የዩኤስ ኤይድ ዋና ኃላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት(ዩኤስ ኤይድ) ዋና ኃላፊ ስኮት ሆክላንደር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱም በክልሉና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት መካከል ያለውን ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ ያካተተ ነው፡፡
በተጨማሪ በክልሉ በውሀ ፤ በእርሻ ልማትና በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ዩኤስኤይድ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችን ለማዳረስ ያለመ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የ‘’ዋሽ’’ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል በይፋ አስጀምሯል፡፡
ፕሮጀክቱ 16 ወረዳዎችን፣ ስድስት ዞኖችን ማለትም ሲቲ፣ ጀራር፣ ፋፋን፣ ሸበሌ፣ ሊበንና ዳዋን ማተቱም ነው የተገለጸው፡፡
ዩኤስኤይድ 44 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ለዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የዋሽ ፕሮጀክት በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ እየተገበረ መሆኑንም በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!