የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ 40 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚገመት 40 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶችን ለጤና ሚኒስቴር በድጋፍ አበረከተ።
ድጋፉ በዋናነት ቫይረሱን ለመከላከል ግንባር ቀደም ሆነው ለተሰለፉ የጤና ባለሙያዎች የሚውል መሆኑ ነው የተነገረው።
ከህክምና መከላከያ ቁሶቹ በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስን ለማከም የሚረዱ ቁሳቁሶችም በድጋፉ ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።
ድጋፉን የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዛፉ እየሱስወርቅ ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።