Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያ ታምርት” የኢንዱስትሪ ንቅናቄ የምክክር መድረክ በደብረ ብርሀን ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ ታምርት” የኢንዱስትሪ ንቅናቄ የምክክር መድረክ በደብረ ብርሀን ከተማ እየተካሄደ ነው።
 
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ÷ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት ባለፉት ሁለት ዓመታት 255 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል ብለዋል።
 
በደብረ ብርሀን ከተማ የጀመረው ክልላዊ ኢትዮጵያ ታምርት መርሀ ግብር በቀጣይም በሌሎች ከተሞች እንደሚከናወን ጠቁመዋል።
 
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት፤ የምርት ማነስ እና የተቋማት ቅንጅት መጉደል ችግርን በመፍታት በኩል ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄ ለውጥ እያመጣ ነው።
 
መንግስት ለባለሀብቱ የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት አሰራሩን ለማዘመንና መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
 
አልሚዎችም በተገቢው ወደ ስራ በመግባት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኢትዮጵያ ታምርትየምክክር መርሀ ግብር ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ አህመዲን (ዶ/ር) ጠቁመዋል።
 
በመድረኩ ባለሀብቶችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
 
በግርማ ነሲቡ
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.