Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለስደተኞች የዲጂታል መታወቂያ መስጠት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬ ለስደተኞች የዲጂታል መታወቂያ መስጠት መጀመሯን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሐሰን አስታወቁ፡፡
 
የዲጂታል መታወቂያ መስጠት መጀመሩም ስደተኞች በብሔራዊ ሥርዓት እንዲካተቱ እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
 
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል÷ የዲጂታል መታወቂያ መኖሩ በተቋማት መካከል የተቀናጀና የተናበበ የስደተኞች መረጃ እንዲኖርና ብሎም የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል፡፡
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ተወካይ አንድሪው ምቦጎሪ÷ ኢትዮጵያ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በብሔራዊ ሥርዓት በማካተት ከምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ሀገር ናት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስደተኞች መብት አክብራ እየሠራች መሆኗን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከ1 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗ ይታወቃል፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.