ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ጀልባ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ጀመረች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው፡፡
ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት ጀልባና ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ በአሶሳ መርከብ ላይ ተጭነው ነው ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት፡፡
ከቀናት ጉዞ በኋላም መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ይጠበቃል መባሉን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ጣናነሽ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ ስትሆን 38 ሜትር እርዝመት እንዳላት ተገልጿል፡፡
በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት እና ለጣና የውኃ ላይ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንደምትሰጥ ተመላክቷል፡፡