በነገው ፋና ላምሮት ስምንት ተወዳዳሪዎች ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ ሁለቱን ምድብ በአንድ በማገናኘት የስምንት ተወዳዳሪዎች ጠንካራ ፉክክር ያስተናግዳል፡፡
ላለፉት 8 ሳምንታት በሁለት ምድብ ተከፍለው ሲወዳደሩ የነበሩት ተወዳዳሪዎች ነገ ሲገናኙ÷ ሄኖክ ብርሃኑ፣ ኃይለየሱስ እሸቱ፣ ራሄል ተሬሳ፣ በረከት ደመወዝ፣ ሀብታሙ ይሄነው፣ ትዕግስት አስማረ፣ ባምላክ ቢያድግልኝ እና ኪሩቤል ጌታቸው ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ተወዳዳሪዎቹ በራሳቸው እና በዳኞች የሙዚቃ ምርጫ በሁለት ዙሮች አቅማቸው ያሳያሉ፡፡
ለ4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የባለተሰጥኦ ድምፃውያን ውድድር 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም አድማጭ ተመልካቹ የነገውን ጠንካራ ፉክክር÷ በፋና ቴሌቭዥን፣ በፋና የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾችን ጨምሮ በwww.fanabc.com ከ6፡00 ሠዓት ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናና እንዲደግፍ ጋብዟል፡፡
በለምለም ዮሐንስ