Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክልሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም አቶ አክሊሉ ታደሰ÷ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸውን ወዳጅነት የሚመጥን የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲኖራቸው መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

ለዚህም ተቋማቸው ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን እንዳረጋገጡ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን በበኩላቸው÷ኤምባሲያቸው አዳዲስ የሩሲያ ባለሀብቶች በግብርና፣ በአውቶምቢል አሴምብሊና ሌሎችም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡም በድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠናና ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመግባት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የቀረቡ መሰረተ ልማቶች ለባለሃብቶቹ ምቹ መሆናቸውንና በጋራ በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.