Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጣሊያን ኢንቨስትመንት ትስስርን የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጣሊያን ኢንቨስትመንት ትስስርን የሚያጠናክር ውይይት ተካሄዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ÷ከጣሊያን ልማት ትብብር ዋና ዳይሬክተር ስቲፋኖ ጋቲ እና ልዑካቸው ጋር የሁለቱን አገራት የኢንቨስትመንት ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

አቶ ታረቀኝ÷ኢንዱስትሪያላዜሽንና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የመንግስት የኢኮኖሚ አጀንዳ ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን በመግለጽ  ተቋማቸውም ለግቡ መሳካት አስፈላጊውን ፖሊሲ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የጣሊያን ባለሃብቶች ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቅሰው÷ሁለቱ አገራት በተለያዩ የልማት እና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ትብብሩ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስቲፋኖ ጋቲ በበኩላቸው÷ግንኙነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል በኢንቨስትመንት አማራጮችና ፕሮጀክቶች ላይ እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡

የጣሊያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የቡና ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራታቸውን በመጥቀስ በቀጣይም በፋሽን፣ በጨርቃጨርቅ እና በሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሰማራት ለዜጎች የስራ እድል የመፍጠርና በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.