Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና አልጀሪያን ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና አልጀሪያን የሁለትዮሽ ግንኙነት በይልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያ እና አልጀሪያን የሁለትዮሽ ግንኙነት በይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ሀገራቱ በጋራ ጥቅሞች ላይ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ አምባሳደር ታዬ ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቡርታ (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.