Fana: At a Speed of Life!

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 202 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ7ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 202 ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ 65 የሕክምና ዶክተሮች፣ 49 ስፔሻሊስት ሐኪሞችና 88 በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮሌጁ ከ13 ዓመታት በፊት የሕክምና ሙያ ትምህርትን መስጠት የጀመረ ሲሆን÷ በዘርፉ በዓመት እስከ 1 ሺህ 500 ተማሪዎችን ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሰብ ስፔሻሊቲ ድረስ እያስተማረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ኮሌጁ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅነት ለማደግ በሕክምናና በትምህርቱ ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት በየጊዜው በማስፋትና በማዘመን ላይም እንደሚገኝ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.