Fana: At a Speed of Life!

በዱቤ መድኃኒት ወስደው ገንዘብ ላልከፈሉ የጤና ተቋማት አገልግሎት አልሰጥም – ጽ/ቤቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዱቤ መድኃኒት ወስደው ገንዘብ ላልከፈሉ የመንግሥት የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማይሰጥ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አግልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዘመን ለገሰ እንዳሉት÷ ተቋሙ ለ570 የመንግሥት ጤና ተቋማት መድኃኒት ያቀርባል፡፡

ተቋማቱ በዱቤ ለወሰዱት መድኃኒት ገንዘብ ባለመክፈላቸው ምክንያት መቸገራቸውን ጠቅሰው÷ እስካሁንም ለጽሕፈት ቤቱ መመለስ የነበረበት 165 ሚሊየን ብር ገቢ አልሆነም ብለዋል፡፡

በመሆኑም ከመጋቢት ወር 2016 ጀምሮ ከሐዋሳ፣ አርባ ምንጭና ነጌሌ ቦረና ቅርንጫፎች ዱቤ ወስደው ገንዘብ ላልከፈሉ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማይሰጡ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.