Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ ዓለም ባንክ ዳይሬክተር ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ ዓለም ባንክ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክን ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ።
 
በዚህ የችግኝ ተከላም የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካሮሊን ተርክን ላለፉት ጥቂት ዓመታት ለኢትዮጵያ ላደረጉት የማያቋርጥ ላሉት ድጋፍ መስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
ተግባራዊነቱ በግለሰብ እና በቤተሰብ ደረጃ የሚፈጸመው እና “ዛፍ በደጃፍ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ዜጎች በቤተሰብ ደረጃ ርቀታቸውን በመጠበቅ የኮቪድ-19ን ከመከላከል እርምጃ ጋር አብሮ እንዲከውኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ማሳሰባቸው ይታወቃል።
 
በዚህ መንገድም ዘንድሮ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅድ ተይዟል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.