Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡ በ“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ በ“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሕብረተሰቡ ባደረገው ድጋፍም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና የትምህርት ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞች እና ጥራት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ታዬ ግርማ ገልጸዋል፡፡

በዚህም 14 ሺህ ትምህርት ቤቶች መጠገናቸውን ነው ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

እንዲሁም ከ1 ሺህ 600 በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ንቅናቄው የትምህርት ቤቶችን ደረጃዎች ለማሻሻል አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ጠቅሰው፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች እድሳት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

ሕብረተሰቡ በጉልበት፣ በዓይነት እና በገንዘብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.