Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ዞኖች በምክክር መድረኩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በምዕራብ እና ምሥራቅ ሐረርጌ ዞኖች በምክክር መድረኩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታና የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩም በወረዳ ደረጃ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ ከ36 ወረዳዎች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች እየተሳተፉ ነው፡፡

በተመሳሳይ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እየተካሄደ መሆኑን ትናንት ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.