Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጉብኝት አደረገ፡፡

ጉብኝቱ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር የሚያጠናክርና ብዙ ልምዶች የተገኙበት መሆኑን የመከላከያ የአዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ምክትል አዛዥና ለትምህርትና ስልጠና ኮሮኔል ተረፈ ጩሪሶ ተናግረዋል፡፡

ኮሌጁ የኢትዮጵያንና ጎረቤት ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ከአጭር ኮርስ እስከ ማስተርስ ዲግሪ እያሰለጠነ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የልዑኩ መሪ ኮሮኔል ጃፋር ረመዳን አርስታይድ በበኩላቸው፥ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን እና በተመለከቱት የኮሌጁ ሥራም መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ከኮሌጁ ጋርም በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ልዑኩ ከ12 ሀገራት የተወጣጡ ወታደራዊ መኮንኖችንና የኮሌጁ ስታፍ አመራሮችን ያካተተ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.