ከ78 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የብሬል መጽሐፍትን እያሳተምኩ ነው – ቢሮው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ78 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ ለአይነስውራን መማሪያና ማስተማሪያ የሚሆኑ የብሬል መጽሐፍን እያሳተመ መሆኑን አስታወቀ፡፡
መጽሐፍቱ በበጀት ዓመቱ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚማሩ አይነስውራን መማሪያና ማስተማሪያ የሚውሉ መሆናቸው ተጠቅሷ፡፡
በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የተዘጋጀው የብሬል መጽሐፍ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች ውጤታማነት ጉልህ ድርሻ እንዳለው መገለጹን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
ለአብነትም ተማሪዎቹ የብሬል ንባብ ክኅሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ በቀላሉ አንብበው እንዲረዱ፣ የቤት ሥራም ሆነ የክፍል ሥራ ከመጽሐፉ በቀላሉ እንዲሠሩ ከማገዝ ባለፈ ትሐዊነትንና የትምህርት ጥራትን እንደሚረጋግጥ ተመላክቷል፡፡