Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ወደ ስደተኞች መጠለያዎች እንዳይገባ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በድንበር አካባቢ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያዎች እንዳይገባ ጠንካራ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ገለጸ።
 
ኢትዮጵያ መጠለያ በመስጠት እያኖረቻቸው የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር ወደ 100 ሺህ ይጠጋል።
 
የኮሮናቫይረስ የሰዎችን ጥግግት የማይፈቅድና በተቃራኒው መራራቅን ተግባራዊ ማድረግን የሚያስገድድ ነው።
 
የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ደግሞ በርካታ ሰዎች በአንድ መጠለያ ተፋፍገው እንዲኖሩ ግድ ይላሉ።
 
ይህ የአኗኗር ሁኔታ ታዲያ ስደተኞች ዓለም አቀፍ ስጋት ሆኖ እየተስፋፋ ላለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል።
 
በመሆኑም ችግሩ ተከስቶ አስከፊ ውጤት ከመከተሉ በፊት የቅድመ መከላከልና የዝግጅት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተሰሩ ስለመሆኑ ተነግሯል።
 
የኢትዮጵያ የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ጫኔ እንደገለጹት ስደተኞቹ የችግሩ ሰለባ እንዳይሆኑ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራዎች ተጀምረዋል።
 
መጪው ክረምት መሆኑን ተከትሎ ስጋቱን በእጥፍ ስለሚጨምረው መጠለያዎችን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ምንጭ፡- ኢዜአ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.