ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በጅማ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የተሳታፊዎች መረጣ ሂደት አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጅማ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የተሳታፊዎች መረጣ ሂደት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በጅማ ከተማ ለ10 ቀናት ሲያካሂድ በነበረው መድረክ ከ7 ዞኖች የተውጣጡ የ114 ወረዳዎች ተወካዮች ተሳታፊዎችን መርጧል።
ከጅማ በተጨማሪ በአዳማ፣ በሀረርና በሻሸመኔ ክላስተሮች የተሳታፊ መረጣ ሲያካሂድ እንደነበር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ከአማራና ከትግራይ ውጭ ባሉ ክልሎችና የከተማ መስተዳደሮች የተሳታፊዎች መረጣ መከናወኑንም ገልፀዋል።
በቀጣይም ከማህበረሰቡ የተመረጡ ተሳታፊዎች በአንድነት በመምጣት በክልል ደረጃ ምክክር እንደሚያደርጉና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ዝግጅት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
በሙክታር ጠሃ እና አሚና አብደላ