Fana: At a Speed of Life!

259 ኢትዮጵያውያን ከኩዌት ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 259 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ከኩዌት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር ዴኤታ ጽዮን ተክሉ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የዳያስፖራ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀምድ ሰኢድ እንዲሁም ሌለች ከፍተኛ የመንግስት ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ በዚህ ሳምንት 1 ሺህ 150 ኢትዮጵያውያን ከኩዌት እንደሚመለሱ ተገልጿል።

በዛሬው እለት ከኩዌት የተመለሱት ኢትዮጵያውያኑ በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ቦታ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ቤተሰቦቸቸው የሚቀላቀሉ ይሆናል።

በፀጋዬ ንጉስ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.