Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለፊቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የኦሮሞ ሕዝብ በሲዳማ ህዝብ በድምቀት ለሚከበረው የፊቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የክልሉ መንግስት በመልዕክቱ ÷ የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ የሆነው የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ትልቅ በዓል መሆኑን አውስቷል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተለያየ ባህል፣ ወግ፣ ትውፊትና ቋንቋ መኖራቸው፣ መጎልበትና መበልፀጋቸው ለሀገር ውበትና ኩራት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ወንድም የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ባህሉንና ወጉን ለማሳደግ እንዲሁም ከሌሎች ህዝቦች ጋር በአንድነትና በወንድማማችነት ለመኖር ሲታገል ቆይቷል ሲል በመልዕክቱ ጠቅሷል፡፡

ከለውጡ በኋላም የራሱን ክልል መስርቶ በተሟላ መልኩ ራሱን በማስተዳደር ባህሉን፣ ቋንቋውንና ወጉን ለማሳደግ መብቃቱን ነው የተገለጸው፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ህዝብ ከሲዳማ ክልልና ህዝብ ጋር በመሆን የተጀመረውን ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት በማጠናከር የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል፡፡

የክልሉ መንግስት በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ በዓሉ የደስታና የአብሮነት እንዲሆንም ተመኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.