በቄለም ወለጋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን ዳሌሰዲ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የደረሰው ትናንት በወረዳው ከባድ ጭነት ተሸከርካሪ (ሲኖትራክ) ከደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ሰርቪስ) ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
በአደጋው ሁለት የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የሰራተኞች ማመላለሻ አሽከርካሪው ሕይወት አልፏል፡፡
እንዲሁም 4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞኑ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በገላና ተስፋ