Fana: At a Speed of Life!

ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለአንድነትና አብሮነት ጽኑ መሰረቶች ናቸው – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለሕዝቦች ዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት ጽኑ መሰረቶች ናቸው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

አፈ ጉባኤው 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልእክታቸውም÷ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለሕዝቦች ዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት ጽንኡ መሠረቶች ስለሆኑ የኢድ አልፈጥር በዓል ሲከበር ለአንድነትና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የሃይማኖቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች የተቸገሩትን በመደገፍና በሕዝቦች መካከል ፍቅርንና መተሳሰብን በማጽናት የበኩላችውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እንዲሁም የተጀመረውን ሀገራዊ ልማት ዳር ለማድረስና የሀገሪቱን ሰላም ለመጠበቅ መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.