Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 393 ሚሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀጣዩ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ393 ሚሊየን በላይ ችግኝ የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዓለምይረጋ ወልደስላሴ እንደገለጹት÷ ለ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስፈላጊው እቅድ ተዘጋጅቶ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም በክልሉ ሁሉም ዞኖች ለቀጣዩ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ393 ሚሊየን በላይ ችግኝ የማፍላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን በተከናወነ ሥራ 328 ሚሊየን ያህል ችግኝ ለቆጠራ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

የችግኝ መትከያ ቦታ በመለየት ረገድም 139 ሺህ ሄክታር የተከላ ቦታ እየተለየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የተዘጋጁ ችግኞች የሚተከሉበት ቦታ፣ ጊዜ እና መሰል ጉዳዮች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የመለየት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ቀደም ሲል ከተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ጎን ለጎን የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን የመቆፈር ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.