Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 688 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 688 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካል 52 ተማሪዎችን በድሕረ ምረቃ እንዲሁም 1 ሺህ 318 ተማሪዎች በዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸው መሆኑ ተገልጿል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሙክታር እንዳሉት÷ መንግስት የትምህርት ዘርፍ የሚታዩ የጥራት መጓደሎችን ለመቅረፍ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው።

ተመራቂዎች የሀገር እድገትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች በሚሰማሩበት የስራ መስክ በታማኝነትና ቅንነት በማገልገል የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እንደ ሀገር የተቀረፁ የለውጥ አጀንዳዎችን በመተግበር ረገድ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው÷ የአካባቢውን ማሕበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከወሰዳቸው 56 የትምህርት መስኮች 50 A+ እና 6A ያመጣው ዳዊት ከተማን ጨምሮ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ምሩቃን የሜዳሊያና ሌሎች ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.