Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.