ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ መሠረታቸውን በደቡብ ክልል ካደረጉ የፓለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መሠረታቸውን በደቡብ ክልል ካደረጉ የፓለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ተወያዩ።
በውይይቱም፣ ከክልሉ መዋቅር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች እና ጉዳዮች ተነስተዋል ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ከደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ዛሬ ባካሄድነው ውይይት፣ የተነሡት ሐሳቦች እና የታየው ግልጽ የውይይት መንፈስ የሚደነቅ ነው” ብለዋል።
በክልሉ የሚኖሩ ሕዝቦችን ልዩ ልዩ ፍላጎት ባማከለ መልኩ፣ ክልሉን እንደገና ለማደራጀት በሚቻልበት መርሕ ላይ መወያየታቸውንም አስታውቀዋል።
“እንዲህ ያሉ ውይይቶች መቀጠላቸው ወደ ተሻለ ጎዳና እንድናመራ እና ዴሞክራሲያዊ እሴቶች እንዲዳብሩ የሚያስችል ነው” ሲሉም ገልፀዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።