Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ሲምፖዚዬም በዘርፉ ያላትን ተሞክሮ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዶሚኒካን ሪፐብሊክ በተዘጋጀው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሉላዊ የአፈፃፀም ድጋፍ ሲምፖዚዬም ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ አካፍላለች፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሲምፖዚዬም ላይ  እየተሳተፉ ነው፡፡

አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ÷ በሲምፖዚዬሙ  የአቪዬሽን ዘርፉን በሚያሳድጉ እና በሚያዘምኑ ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ  በርካታ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ የአቪዬሽን ዘርፍ ስኬቶች እንዲሁም የመጪው ዘመን አቪዬሽን እድገት ማሳያዎች እየቀረቡ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያም የአቪዬሽን ዘርፍ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት ላይ ያለውን አስተዋፅኦ በተመለከተ ያላትን ተሞክሮ  ማካፈሏን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.