የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን ቤቶች አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በኮየ ፈጬ እና በቃሊቲ ሳይቶች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስተላለፈ።
በቤቶቹ ማስተላለፍ በስነ-ስርዓት ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ቤቶቹ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
በመራኦል ከድር